ከኢትዮጵያ መፍረስ በፊት የእኔን መፍረስ የማስቀድም – ኩሩ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣

እትብታችን በሸዋ ምድር ለተቀበረ፣
….. ዘመዶቻችን ጎጆ ቀልሰው፣ ጤፍ ዘርተው፣ እሸት እንኩቶ በልተው፣
መንገደኛውን ከሩቅ ጠርተው፣
ከተገኘ ወተት ከጠፋ አሬራ፣
ከተገኘ ጨጨብሳ በእርጎ …. ካልተገኘ የስንዴ እንጀራ፣
በደህናው ቀን ጠላ ካልተገኘም ቅራሪ …
ጋብዘው … ሲሸኙ አይተን ያደግን …።
*****************
….. ሶማሊያ ሐረር ደጃፍ ድረስ በትዕቢት ተወጥራ ብትመጣ እርሻቸውን ጥለው ታጠቅ ጦር ሰፈር የከተቱት …
ተኝቶ መዋጋትን ከፍርሃት ቆጥረው …
የሶማሊያ ወራሪ ታንክ ላይ ዘለው ከነ ቦምባቸው የወጡት …
ከትግራይ አስገንጣዮች እና ከኤርትራ ገንጣዮች ጋር ተናንቀው የወደቁት …. … አጥንታቸው የሰሜን ኢትዮጵያን ላለበሰው ዘመዶቼ ክብር ያለኝ ኩሩ ኦሮሞ ኢትዮጵዊ ነኝ።
….. ኢትዮጵያ ካልፈራረሰች ደስታ የሌላቸው …
ስመ-ኦሮሞ ውስጠ-ከሐዲዎች ወገን ያልሆንኩ፣
አሁንም ኩሩ ኦሮሞ ኢትዮጵዊ ነኝ፣።
***********
ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል በኩራት ነው።
አገሬ ስላት ሳግ እየተናነቀኝ በደስታ ነው።
ብችል ብሞትላት ደስታ እንጂ ሐዘን አይሰማኝም።
….. ኦሮሞነትን የኢትዮጵያዊነት ጠላት የሚያደርጉ፣
ክህደታቸውን ሳያፍሩ ለመናገር የሚደፍሩበት ዘመን ከሆነ፣
በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ ብዙ ኦሮሞዎች እንዳሉ እንነግራቸዋለን።
….. በብሔረሰብ እና በቋንቋ፤
በወንዝ እና በመንደርተኝነት መኩራት አያስፈልግም እንጂ፣
እኛም ኩሩ ኦሮሞ-ኢትዮጵያውያን ነን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች።
አሜን።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s