የተመድ ሰራተኞች ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ

ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች በሚቀጥሉት ቀናት በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ሰልፍ በሚካሄድባቸው ቦታዎች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታና ደህንነት ክፍል ባለስልጣን ገለጹ።

UNDSS

ማርኮ ስሞልነር የተባሉ የተባበሩት መንግስታት የደህንነትና የጸጥታ ክፍል ባለስልጣን ባሰራጩት የኢሜይል መልዕክት፣ በሚቀጥለው ቅዳሜና እሁድ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የዞንና የወረዳ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ሊደረጉ ስለሚችሉ፣ የተመድ ሰራተኞች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል።

በማህበራዊ መገኛኛ ብዙሃን የተላለፈው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ተከትሎ የተሰራጨው ይኸው የኢሜይል ማሳሰቢያ፣ በሁሉም የኦሮሚያ ክፍሎች የወረዳና የዞን ከተሞች የትራፊክ መጨናነቅና እስከሞት ሊደርስ የሚችል ግጭት ሊከሰት ይችላል በማለት ማሳሰቢያን ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስና የጸጥታ አስከባሪ ሃይላት ሰላማዊ ሰልፍ በሚደረግባቸው ቦታዎች በብዛት ሊንቀሳቀሱ ስለሚችሉ፣ በሰላማዊ ሰልፈኛውና በጸጥታ ሃይሎች ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲል ግምቱን አስቀምጧል።

ለውጭ ዜጎችና ለተባበሩት መንግስታት ሰራተኞች ከሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች ማስፈራሪያ ወይም ዛቻ እንዳልተላለፈ በኢሜይላቸው ያመለከቱት ሚስተር ስሞልነር፣ ሆኖም ግን የተመድ ሰራተኞች የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ካናዳውያን በኦሮሚያ የዞንና የወረዳ ከተሞች ከሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ከመሳተፍ እንዲታቀቡ የካናዳ መንግስት ጠይቋል። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች  በሚደረጉ ታላላቅ ስብሰባዎችን ዜጎቹ እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ የሚጓዙበት አካባቢ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ማረጋገጫ ካላገኙ አደጋ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉም አስጠንቅቋል።

በአንዳንድ ቦታዎች እስከ ህይወት መጥፋት ሊያደርሱ የሚችሉ ግጭቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግምቱን ያስቀመጠው የካናዳ መንግስት መግለጫ፣ ዜጎቻቸው ሰላማዊ ሰልፍ በሚደረጉ ቦታዎችና ሰዎች ሰብሰብ ብለው በብዛት በሚቆሙበት ቦታ ጭምር እንዳይገኙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የካናዳ መንግስት ካናዳውያን በፌስቡክም ሆነ በሌሎች ድረገጾች የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ከመጦመር እንዲታቀቡ፣ ሆኖም በዚህ ጉዳይ ተሳትፈው ከተገኙ በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች ለእስር ሊዳረጉ እንደሚችሉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

መግለጫው ካናዳውያን  በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎችን እንዲከታተሉም አክሎ ተጠይቋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s