ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መንግስት በሚቀጥለው አመት በኤርትራ መንግስትና በተቃዋሚዎች ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል አሉ

ESAT_Top_Logo_Banner_32መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-የመጨረሻ የስራ ዘመናቸውን ዛሬ ለጀመሩት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት የመክፈቻ  ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መንግስት አምና እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ከኤርትራ

መንግስት ለሚሰነዘር ማንኛውም ትንኮሳ ተመጣጣኝ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል። የኤርትራ መንግስት አስታጥቆ የላካቸውን የ ግንቦት7 ፣ ኦብነግና ኦነግ ጥቃቶችን መከላከላቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በዚህ አመትም ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

ዶ/ር ሙላቱ  የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በዘረኝነትና በጥላቻ ተነሳሰስተው ተቃውሞ እንደሚያነሱም ገልጸዋል። መንግስት  በአንድ በኩል ተቃዋሚዎች ጉልበት የላቸውም እያለ በሌላ በኩል ደግሞ ጥቃታቸውን ሲመክት መቆየቱንና ተመሳሳይ እርምጃ በዚህ

አመትም እንደሚወስድ መግለጹ እርስ በርስ የሚቃረን መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ዶ/ር ሙላቱ መንግስት ለኤርትራ መንግስት ተደጋጋሚ የድርድር ጥያቄ ሲያቅርብ መቆየቱንም ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ችሎት ለኤርትራ መንግስት ሲሰልሉ ተገኝተዋል በተባሉ ሶስት ኢትዮጵያውያን ላይ እንዲከላከሉ ወስኗል። በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉለመዲ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ነጋሲ ብርሃነ ሹማይ፣ ተበጀ

በረኸ እና ብለጽ ገብረጻድቃን ዛላንበሳ ስለሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ለኤርትራ መረጃ ሰጥተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።  ግለሰቦቹ ከኤርትራ መንግስት ስልጠናና ገንዘብ እንደተሰጣቸውም ተገልጿል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሾች እንዲከላከሉ ውሳኔ አስተላልፏል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s