ለምን ኢሳት የኔ!

913_661258187269555_1423144382_nለምን ኢሳት የኔ!

 በአሁኑ ሰአት ሃገራችን ኢትዮጵያ በአምባገነኖች ስር የወደቀች ሃገር መሆኗን ሁላችንም እናውቃለን ወያኔ የኢትዮጵያዊነትን ታሪክና ባህልን የማጥፋት እቅዱን መፈጸም እና የህዝብን የሀገር ሀብት መዝረፍ በስፋት ተግበራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል:: የወያኔ ፈላጭ ቆራጭነት የኢትዮጵያ  ሕዝቦችን በዘር: በብሄር: በቋንቋ: በሀይማኖት: ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ አንድነት እንዳይፈጥሩ: ማህበራዊ ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹ በጋራ እንዳይፈቱ: የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብት በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ
                                                                                                                          ሐና ገለታ ከኖርዌይ
ማድረግ: ለግል ጥቅማቸው ያደሩትን አንዳንድ  ግለሰቦች እና ሀይማኖተኞች
አቅፎ እምነትህ ባህልህ እና ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅን
ዋንኛ አላማዉ አድርጎ ለአመታት ተያይዞ ገፍቶበታል።

 ወያኔ ህገመንግስታዊ መብቶችን በመናድ የመናገር:የመፃፍ: የመሰብሰብ:  የመደራጀት:በነፃነት ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የመግለጽ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን: የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ ተፈፃሚ እንዲሆን በማድረግ የሕዝብን ነፃነት በመግፈፍ እንደ አፓርታይድ ስርአት ሕዝብን እንደ ዜጋ መብቱን ከማስከበር ይልቅ እኔ አውቅልሃለው በሚል  ዜጎችን ከተወለዱበት ከኖሩበት ስፍራ ማፈናቀል ንብረትን ማዉደም ማሰር ማንገላታት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደል የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረትንና ሀብትን ለባዕዳን አሳልፎ መስጠት ለግል ጥቅም ማግበስበስ በሙስና እና በዘረፋ ሕዝብን ለድህነት ለርሐብ አጋልጦታል። ይሕ ሁሉ አስከፊ እና ብልሹ አሰራር የመልካም አስተዳደር እጦት ዜጎች ለስደት ተዳርጎዋል።  እንዲሁም በስደት በረሀ መቅረት መበታተን የኢትዮጵያ ሕዝብ እጣ ፈንታ እስኪመስል እና ተሰደው በሚኖሩበት ምድር የሰብአዊ መብት ክብራቸው ተዋርዶ ማየት የቅርብ ጊዜ የሰቆቃ ትዝታችን ሆኗል።ይህን ሁሉ የወያኔ ግፍ ፍንትዉ አርገን ለመስማታችን እድሜ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንደበት አይንና ጆሮ ለሆነዉ ኢሳታችን።

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ይህ የግፍ አገዛዝ ማብቃት አለበት፤ በሁሉ አቀፍ ዴሞክራስያዊ ሥርዓት መተካት አለበት ካለ ቆይቷል። ኢትዮጵያ በዚህአስከፊ ሁኔታ ከቀጠለች፤ለግዛታዊ አንድነቷና ለሕዝቧ ሰላም፤ አብሮ መኖር፤ ዘላቂና ፍትሃዊ እድገት ያሰጋታል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህ አይነት አምባገነንነት እንዲቀጥል አይፈልግም፤ አይፈቅድምም። እናም

ነፃ ሚዲያ ለአንድ ሀገርና ህዝብ ለዉጥ ቁልፍ እና መሠረታዊ የሆነ ነገር ነዉ።አምባገነን ስርአት ህወሀት ወያኔን ጨምሮ ይህ አይዋጥላቸዉም። ነገር ግን የኔ ኢሳት በተቜቁዋመ በአጭር ጊዜያት ዉስጥ እድሜ የለሹን ኢቲቪ ባደባባይ ዉሸታም አስብሎ የኢትዩጵያን ህዝብ ከዉስጥ እና ከዉጭ ያሉትን የነፃነት ሲቃ እያስተጋባ ይገኛል። ዛሬ ወያኔዎች የነፃ ሚዲያን መጨረሻ ጠንቅቀዉ ስለሚያውቁ ሳንተኩስባቸዉ ያለሳንሱር ተጠራርተን በ የኔ ኢሳት ግባተመሬታቸዉ እዳይፈፀም ያየ የነካ የሚል የሽብርተኛ ምላሳቸዉ እየፈጃቸዉ ነዉ።

ወያኔም ይጮሃል የኔም ኢሳት ይቀጥላል ነፃነታችንም እዉን ይሆናል።

ይህ ዛሬ እዚህ የኔ ጉዳይ ብሎ ያሰባሰበን የነፃነት ለዉጥ ጥማታችን  ነዉ ስለሆነም  ኢትዮጵያ ውስጥ የተሻለ ስርአት ለመመስረት እና ለውጥ ለማምጣት መፍትሄ ያለው በእጃችን ነዉ ይኸውም የኢትዮጵያን አንድነት የሚያፈርስ አመለካከትን ወዲያ ጥለን በአንድነት መታገል ስንችልና ነፃሚዲያ ሲኖረን ነዉ ብዬ አምናለሁ ለዚህም ምሳሌ ካስፈለገ የኢሳትን እዉነትና የወያኔን አረመኔያዊ ዉሸተኛነት ብሎም የኢትዮዽያን ህዝብ እዉነትን ሰምቶ ከዉስጥም ከዉጭም ከዳር ዳር አንድ ላይ ሆ ብሎ ለመቆሙ ከመለስ ሞት እስከ ሠማያዊ ፓርቲ  በ 4ኪሎ ከ4 ኪሎ እስከ ሳዉዲ አረቢያ የወገኖቻችን ዉርደት ከሳዉዲ የወገኖቻችን ዉርደት እስከ ዲያስፓራ ሀገራዊ አንድነት በወገን ዉርደት ብሎም ለነፃነት ኢሳት ያደረገዉ አስተዋእፆ በቂ ማስረጃ ነዉ።

ስለዚህ ሳንተኩስ ወያኔን ለማስወገድ ኢትዮዽያችን እና ህዝቦቿን ነፃ ለመዉጣት ነፃ ሚዲያ እሱም ኢሳት።

ስለዚህ  ኢሳት የኔ!!!

hana_geleta@yahoo.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s