መንግስት በአገሪቱ እየታየ ላለው ረሀብ በቂ ዝግጅት እያደረገ አለመሆኑን መረጃዎች አመለከቱ::

ESAT_Top_Logo_Banner_32የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛ የግብርና ምርት  እንደተገኘ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ካላገኙ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ መረጃዎች አመልከተዋል። የዓለም ባንክ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በመግብ ለስራ የታቀፉ ዜጎችን ሳይጨምር ከ3 ሚሎዮን ያላነሱ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በምስራቅ አማራ፣ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ በአፋር እና ኦሮምያ የተከሰተውን ረሀብ ለማስታገስ ከ400 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ እርዳታ ያስፈልጋል።

የአለማቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ አነስተኛ በሆነበት ሁኔታ በዚህ አመት ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ነው ባለሙያዎች ያስጠነቀቁት። የኢትዮጵያ መንግስት ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ረሀብ በመደበቅ ላይ ነው ያሉት ወገኖች፣ በረሀብ የተጎዱት ዜጎች ትክክለኛ አሀዝ ከተጠቀሰው ቁጥር በእጅጉ እንደሚልቅ እየተናገሩነው።

ኤን ቢ ሲ በቅርቡ ባወጣው ዘገባ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን የሞት ደመና እንዳንዣበበባቸው ገልጿል። ከ20 አመት በፊት አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስት ጊዜ ሲበላ ማየት እንደሚፈልጉ ፣ ከ3 አመት በፊት ደግሞ ኢትዮጵያን በአምስት አመታት ውስጥ በምግብ ራሱን ለማስቻል እቅድ መታቀዱ ተገልጾ ነበር። አሁን ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክትቱት ከ23  አመታት የውጭ እርዳታ በሁዋላ አገሪቱ ቀጣይ አመታትንም ከእርዳታ ስንዴ አትላቀቅም።

source/ethsat.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s