የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት በሰኔ ወር መጨረሻ ( July, 2013) ለ 2013) ለሚያካሂደውና አምባገነኑን ሥርዓት በሽግግር መንግሥት ለመተካት የሚደረገው የምክክር ጉባዔ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው።

Ethiopian National Transitional Council  ENTC
P.O.Box 9929
Alexandria, VA 22304
Tel: 1-571-335-4637
Tel: +44-7958-487-420
Email: contact@etntc.org
Website: http://www.etntc.org
June 14, 2013
ጋዜጣዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት በቅርቡ ለሚያካሂደውና አምባገነኑን ሥርዓት ለማስወገድና
ለመተካት በሚደረገው ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባዔ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው። የምክክር ጉባዔው
የተጠራው ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዴት ወደ ዴሞክራሲአዊ ሥርዓት እንደምትሸጋገር በሚቀርቡ የተለያዩ
አማራጮችና ሃሳቦች ላይ ለመወያየት ሲሆን፣ ጉባዔውም የሚካሄደው በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ላይ ሰኔ
25 እና ሰኔ 26 ቀን 2005 (July 2 and 3, 2013) ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤትም
መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ላይ ሰኔ 27 እና ሰኔ 28 ቀን 2005 (July 4 and 5, 2013) ያካሂዳል።
የሽግግር ም/ቤቱ የአካባቢ ምክር ቤት ተወካዮች፣ የተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና
ስብሰባውን ለመካፈል የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ሰኔ 24 ቀን 2005 (July 1, 2013)
ይገባሉ። (ይህ የምክክር ጉባዔ ክፍት የሚሆነው ለተጋባዥ እንግዶች ብቻ ነው)።
በእዚህ እጅግ አስፈላጊ የምክክር ጉባዔ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑት የሀገሪቷ ጉዳይ የሚያገባቸውና ከኢትዮጲያ
የተለያዩ ሕብረተሰብ የተውጣጡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ናቸው። እነዚህ ተቋማትና ግለሰቦች፣ በኢትዮጲያ
ያለውን ጨካኝና አምባገነን ሥርዓት እንዴት እንደሚወገድና በምትኩም ሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ የሽግግር
መንግሥት እንዴት እንደሚቋቋም ሃሳባቸውን በማቅረብ ውይይት ያካሂዳሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሰኔ 2004 (July 2012) የተቋቋመ ሲሆን፣ ካለው ዋና
መሰረታዊ ዓላማ እንዱ ሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ የሽግግር መንግሥት የሚቋቋምበትን መንገድ ማመቻቸት
ነው። ምክር ቤቱ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የአካባቢ ምክር ቤቶችን በአገር ውስጥና በውጭ አገር
በማቋቋም እየታገለ ሲሆን፣ ከሕዝብ ጋር፤ ከተለያዩ ህዝባዊ ተቋማትና ድርጀቶች ጋር ደግሞ የሽግግር
መንግሥትን አስፈላጊነት እየተነጋገረበት ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪ፣ የሽግግር ምክር ቤቱ በሀገራችን
ኢትዮጲያ ውስጥ መልዕክቱን ለሕብረተሰቡ እያስተላለፈ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጲያ ውስጥ
የሚገኙት የሽግግር ምክር ቤቱ አባላት በራሪ ወረቅት በመበትንና ፖስተር በመለጠፍ የሥርዓት ለውጥ
ጥያቄውን እያሰራጩ ነው።
አንድነት ሃይል ነው!!
የሽግግር ምክር ቤቱ አመራር

source/maledatime

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s