ነጋ ደግሞ !

ነጋ ደግሞ !

 

ላስታምም የሆዴን ጩርር ….. ርታ፤

ላዳምጥ የወስፋቶቼን ጩኸት ጫጫታ፤

የማያቋርጥ የረሃብ ሳል ልስል፤

እሹሩሩ እያልኩ ረሃብን ላባብል፤

ልደማ ልቆስል ልገዘገዝ በችጋር፤

በቁም ሞቼ – ላልኖር ስኖር፤

በብርሃኗ ሳላጌጥ – ጮራዋ ለኔ ሳይፈነጥቅ፤

ነጋ ደሞ ! …… ሌሊ ቀን – ፀሐይ ወ’ታ ልትጠልቅ ::

ነጋ ደግሞ !

ጅራፍ ሆኖ የሰው ዓይን ሊገርፈኝ፤

ማጣት መስታወት ሆኖ የሰው እጅ ሊያሳየኝ፤

ሊያደርገኝ ቀላዋጭ የበይ ተመልካች ፤

የገዛ አገሩ ሃብት ተመጽዋች፤

ደሞ ነጋ !….. የማልበላውን ምግብ ላሸት፤

ሲጎርሱ ሲጎራረሱ ልመለከት፤

ባልበላሁት ምግብ ምች ሊመታኝ፤

እነሱ በበሉ እኔን ሊያገሳኝ ::

ነጋ ደግሞ !

በነ እንቶኔ ሙዚቃ፤

ጆሮዬ ሊደቃ፤

የጆሮዬ ብራና ሊጠለዝ፤

እንደከበሮ ሊነረት ሊጦዝ፤

በነሱ ጉሮሮ ውስኪ ሲንቆረቆር፤

እነሱ በጠጡት እኔ ልሰክር ::

ደሞ ነጋ ! … ተሽሞንሙነው ለብሰው ሊወጡ፤

ሊያምርባቸው በኔ ስቃይ – በኔ ማጣት ሊያጌጡ ::

ነጋ ደግሞ !

የግፍ ጽዋ ሌጨለጥ፤

የበደል እንቆቆ ልውጥ፤

በረሃብ ጅራፍ ልገረፍ፤

በብርድ ቆፈን ልንዘፈዘፍ፤

ከአገሬ – ከትውልድ መንደሬ ልነቀል፤

ትውልድ ላልተካ ዘር ሆኜ ላልበቅል ::

ገና ከጥዋቱ በጨቅላነት ልቀጭ፤

ሊመነገል ስሬ ሊቀጭጭ፤

ነጋ ደሞ ! ….. ሌላ ቀን -ፀሐይ ወ’ታ ልትጠልቅ፤

በብርሃኗ ላላጌጥ – ጮራዋ ለኔ ላይፈነጥቅ ::

ነጋ ደግሞ !……. ሌላ ቀን…… !

በፍትህ እጦት፤ በኑሮ ውድነትና፤ ከሚኖሩበት ቦታ በመፈናቀል፤ ለሚሰቃዩ ወገኖቼ ማስታወሻ ትሆን ዘንድ የተቋጨች:: መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም.ተጻፈ (March 21/ 2014)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s