ነፃነት የሌለበት አገር ጨለማ ነው

የሰላማዊ ሰልፍ ደማቅ መፈክር ስሜትን የሚነካ ሰላማዊ ሰልፍ!!! የኑሮ ውድነት ያጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል!! ህገ መንግስቱን የሚፃረሩ አፋኝ አዋጆች ይሻሩ፣ይሰረዙ !!! በህገ መንግስቱ የሌለውን የሃይማኖት ጣልጋ ገብነት እናወግዛለን!!! እኛስ ኮራን በናንተ!! … ብለናል! … እውነት ዛሬ ይህንን የተቃውሞ ሰልፍ ያስተባበረው ሰማያዊ ፓርቲ ከሰማይ የወረደ ነው የመሰለኝ!! ግንቦት 25 2005 አኮራሽን!!! አንድ እናት እያለቀሱ የሚናገሩት አገራችን እንደ ዳቦ አትፈራርስም በአገራችን ሰላም አጣን! የኢትዮጵያ ህዝብ ለነፃነቱ አበል አያስፈልገውም !!! ያለ አበል ያለ ቲሸርት በየቀበሌው ቡና ጠጡ የሌለበት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ተብሎ እቤቱ ድረስ ያልተጨቀጨቀ ይህ ህዝብ እውነተኛው ኢትዮጵያዊ ነው። በጥይት በዱላ አይገዛም አገር!!!!! እንዴት ደስ ይላል ስንት አመት ያረገዝነውን ብሶት ለመውለድ እየሄደ ያለው ህዝባችን !!! ምንም እንኳ ወያኔ ሕዝቡን እንደ ሁለተኛ ዜጋ አድርጎ ቢያስፈራራውና ቢያሸማቅቀውም ጨዋው ያገሬሰው ለሃገሩ እና ለህዝቡ ያለውን ብሶት በአደባባይ በወያኔ አገዛዝ ለይ ያለዉን ተቃውሞ ለመግለጽ ዝምታዉን ሰብሮ ስለ ነፃነት ዘመረ!

ነፃነት፤ነፃነት፤ነፃነት፤ነፃነት፤ነፃነት፤ነፃነት፤

netsanet

‘ ክብር ለህዝባችን!’
ከዚህ በላይ ምን አለ!!
እኛ ኢትዮጵያዊያን ታጋሽ እንጂ ፈሪ አይደለንም! ዜጎች በፍርሃት የሚኖሩበት ዘመን ይብቃ! ኢትዮጵያዊ ጨዋ ህዝብ መብቱን በሰላማዊ መንገድ የሚጠይቅ! በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ እናት አገር ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ!!! ደስ ሲል በወገኔ ኮራው! ጭቆና ይጥፋ! ወኔ የሌለው የአገር ሸክም ነው! መማር ያስከብራል አገርን ያኮራል! እማማ ኢትዮጵያ በቅርብ ቀን ከአንባገነኑ ከወያኔ መንግስት ነፃ ትወጣለች በልጆችዋ!! እኛ ኢትዮጵያኖች በዘርና በሃይማኖት አንከፋፈልም! እኩልነት፣ተስፋ፣ፍቅር፣አንድነት የታየበት ሰላማዊ ሰልፍ ነው።

ኢቲቪ ውሸታም,,,,,,,,,,,,,,,,, ደስ ሲል!!! “አንለያይም አንለያይም… መቼም አንለያይም አንለያይም!” ፍትህና ነፃነት እንፈልጋለን!

‹‹ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ?›› ብሏል ያ ምርጥ ልጅ፡፡ ‹‹አንቺም በሃይማኖትሽ እኔም በሃይማኖቴ አብረን እንጮሃለን እሰኪከበር መብትሽ፣ እስኪከበር መብቴ››…… ……… ብለን ብንቀጥልበትስ የሚከፋው ይኖር ይሆን?!

*ከአሁን በኋላ*
ፍርሃት ይለቀናል! መብታችንን እናስከብራለን! ስለ ነፃነትና እኩልነት እንዘምራለን! የህዝባችን እኩልነት ይሰፍናል! የስልጣን ባለቤት ህዝብ ይሆናል! የሐይማኖት እኩልነት ይከበራል! ሰዎች በፈለጉበት ቦታ ተዘዋውረው ልጅና ሀብት አፍርተው መኖር ይችላሉ፣የነፃው ፕሬስ ይከበራል! ህዝባችን ፍትህ ያገኛል! ሰው በሰውነቱ እንጂ በዘሩ አይከበርም! የንፁሃን ደም ያፈሰሱትን ለህግ አሳልፈን እንሰጣለን! የመረጥነው ድምፅ ይከበራል! ድል ለሰፊው ህዝብ ውድቀት ለሆድ አደሮች!!

በመጨረሻም ሆነ
=> ሰላማዊው ሰልፍ ተደረገ ጥያቄዎችም በሰላም ተጠየቁ ሕዝብም ሠላምን ለመንግስት አስተማረ ሰሚ መንግስትም ይሥጠን አለን::
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s